ወቅታዊ ጉዳዮች

... ከውድድር ውጪ ሌላ መንገድ የለንም...

... ከውድድር ውጪ ሌላ መንገድ የለንም...
ጓድ ዶክተር ካሱ ኢላላ 

 


እያንዳንዱ ቀን አዳዲስ ነገሮችን እየወለደ ነው፡፡ ያ ደግሞ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ መንደራችን ላይ ሆነን ስናየው ትንሽ ይመስለናል፡፡ ተለቅ አድርገን ስንመለከተው ግን ሁኔታው ቀላል እንዳልሆነ መገመት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ወደ ውስብስብ ነገሮች እየገባን ስንሄድ ደግሞ ሌላ ተጠባቂ ነገር አለ፡፡ ይህን ውስብስብ ነገር ችለነው ብቻ ሳይሆን አሸንፈነው ወደ ብልጽግና መሄድ አለብን፡፡ ድህነትን በፈጠነ መንገድ ታሪክ አድርጎ የመሄድ ነገር እንዳለ ሆኖ ወደ ብልጽግና መሄዱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ውድድር ውስጥ በመግባት ነው የሚረጋገጠው ፡፡ ከውድድር ውጪ ሌላ መንገድ የለንም፡፡ ዓለም በዛ አይነት መድረክ ውስጥ ነው ያለችው፡፡