ወቅታዊ ጉዳዮች

...56 መሆን አይከለክለውም፡፡ አምስት ብቻ መሆንም ዋስትና አይሰጠውም...

...56 መሆን አይከለክለውም፡፡ አምስት ብቻ መሆንም ዋስትና አይሰጠውም...


ብዙ ብሄሮች ብሄረሰቦች መሆናችን ለመበታተን በምንም መልኩ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ የመበታተን አደጋ ሊሆን የሚችለው ይሄን ብዙሃነታችንን በአግባቡ ማስተናገድ ካቃተን ነው፡፡ ይሄን ብዙሃነታችንን በፈጣን ልማት ማጀብ ካቃተን፤ ይሄን ብዙሃነታችንን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ማስተዳደርና ማስተናገድ ካቃተን ነው፡፡ ለዚህም 56 መሆን አይከለክለውም፡፡ አምስት ብቻ መሆንም ዋስትና አይሰጠውም፡፡ 
ዋስትናው ምንድን ነው ከተባለ በሀገር ደረጃ፣ በክልል ደረጃ፣ በየደረጃው በአንድነት ለመኖር የመጀመሪያው ዋስትና ፈጣንና ፍትሃዊ ልማትን ማረጋገጥ ነው፡፡ ለምንድን ነው ፈጣን ልማትን ማረጋገጥ የአንድነትና የአብሮነት ዋስትና የሚሆነው ? ፈጣን ልማት የእያንዳንዱን ሰው ህይወት የመጥቀም የመቀየር ጉዳይ ነው፡፡ የተጠቀመ፣ ህይወቱ የተቀየረ ሰው በዛ በሚጠቅመውና በሚቀይረው ሥርዓት ላይ ቅራኔ ልይዝ አይችልም፡፡ ቅራኔ ካልያዘ ይበልጥ እንዲጠናከርለት፣ እንዲሰፋለት ይፈልጋል፡፡ እኩልነቱ እንዲረጋገጥለት ይፈልጋል፡፡ ሰብአዊ ክብሩ ፣ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥለት ይፈልጋል፡፡ ሰብአዊ ክብርን ያረጋገጠ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ፣ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እኩል ማገልገል የቻለ፣ ያለህን ነገር በፍትሀዊነትና በግልጽ መሥፈርት እንደምትጠቀም፣ እንደምትከፋፈል ማሳየት የሚቻልበት ሁኔታ ካለ አብረህ ካምትኖረው ህዝብ ለምንድነው የምትነጠለው ? ስለዚህ እነዚህ ናቸው ዋስትናዎቹ፡፡ እነዚህ ካልተሳኩ ግን አምስትም ሶስትም ሊበተን ይችላል ፡፡ ምክንያቱም እኩል ተጠቃሚነት ከሌለ ቅራኔ ይፈጠራል፡፡ ቅራኔ ግጭትን ይወልዳል፡፡ ግጭት ደግሞ መበተንን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያው ፈጣን ልማትን ማረጋገጥ ነው፡፡ ፈጣን ልማቱ ደግሞ ዝም ብሎ ለጽድቅ አይደለም፡፡ ፈጣን ልማቱ ለይስሙላ የሚሠራ አይደለም፡፡ ሰዎችን ለመጥቀም ነው፡፡ ህዝቦችን ለመጥቀም ነው ፡፡
የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበር ጓድ ሺፈራው ሽጉጤ