ወቅታዊ ጉዳዮች

የደኢህዴን ምስረታ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል በትግራይ ክልል

የደኢህዴን ምስረታ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል በትግራይ ክልል ለደኢህዴን መመስረት እርሾ የሆነው የስምጥ ሸለቆ ታጋዮች መሸጋገሪያ ማህበር በተመሰረተበት በማይዒባራ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከብሯል፡፡


የአካባቢው ህዝብ ለስምጥ ሸለቆ ታጋዮች ማህበር ምስረታ ያደረገውን አስተዋጽኦ ለመዘከር ደኢህዴን ያስገነባው ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት /ከ1-8 / 25ኛ ዓመት በዓሉን አስመልክቶ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

ታህሳስ 7 ቀን 1983 "የስምጥ ሸለቆ ታጋዮች መሸጋገሪያ ማህበር" የተመሠረተበት ቦታም በበዓሉ ታዳሚዎች ተጐብኝቷል፡፡ 
በበዓሉ ላይ የስምጥ ሸለቆ ነባር ታጋዮችና የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ አካላት እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፏ፡፡